Search

የዴቪድ ራያ ጉዳት እንደሰጋነው ከባድ አይደለም - ሚኬል አርቴታ

ሰኞ ኅዳር 14, 2019 26

ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ የገጠመው ጉዳት መጀመሪያ ላይ እንደተሰጋው የረዥም ጊዜ እረፍት የሚያስከትል ከባድ ጉዳት እንዳልሆነና ቀዶ ጥገና እንደማያስፈልገው የአርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተናግሯል።

ዴቪድ ራያ አርሰናል ቅዳሜ ዕለት ከኒውካስትል ጋር በነበረው ጨዋታ ላይ ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ መውጣቱ አይዘነጋም፡፡

ግብ ጠባቂው በነገው ዕለት ከዶርትሙንድ ጋር በሚደረገው የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ እንደማይሰለፍ አሰልጣኙ ቢጠቁምም፣ የተደረጉ የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ምርመራዎች ውጤት ግን እጅግ ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጿል።

አሰልጣኝ አርቴታ አክሎም፣ «ጉዳቱ ያን ያህል አሳሳቢ አይመስልም። ጉዳቱ በተከሰተበት ቅጽበት የነበረበትን ከፍተኛ ህመም ስናይ በጣም ተጨንቀን ነበር። ዶክተሩ እንደነገረኝ ጉዳቱ ትንሽ ውስብስብ ቢሆንም፣ ከጠበቅነው በላይ ቀለል ያለ ሆኖ ተገኝቷል» ሲሉ አስረድቷል።

አርሰናል ከፊቱ ከሚጠብቋቸው ወሳኝ ጨዋታዎች መካከል ከማንቸስተር ሲቲ ጋር የሚያደርገው ፍልሚያ ይገኝበታል።

ራያ ለዚህ ጨዋታ ለመድረስ ያለውን ዕድል በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄ አርቴታ የመጨረሻውን ውሳኔ በነገው ምርመራ እንደሚረጋገጥ ጠቁሟል።

«ነገ ተጨማሪ እና ዝርዝር የህክምና ምርመራዎችን እናደርጋለን» ያለው አሰልጣኙ፣ «የጉዳቱን ትክክለኛ መጠን ለማረጋገጥ እና ስለ ማንቸስተር ሲቲው ጨዋታ ተሳትፎው እርግጠኛ ሆኖ ለመናገር የነገውን ውጤት መጠበቅ አለብን፤ ከዚያ በኋላ ሁሉንም ነገር እናውቃለን» ሲል ተናግረዋል።

አርሰናል ነገ ምሽት 5 ሰዓት ላይ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በሜዳው ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ ጋር ይጫወታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: