የኢትዮጵያ አየር ኃይል የዘመኑን የቴክኖሎጂ አቅሞችን በመታጠቅና የሰው ኃይሉን በማብቃት በሀገራችን ላይ የሚቃጡ ጥቃቶችን በማክሸፍ ታሪክ እየሠራ እንደሚገኝ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ።
ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ የአየር ኃይል የ91ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበርን አሥመልክተው በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም፣ 91 ዓመታትን በድል የዘለቀው የኢትዮጵያ አየር ኃይል የዘመኑን የቴክኖሎጂ አቅሞችን በመታጠቅና የሰው ኃይሉን በማብቃት በሀገራችን ላይ የሚቃጡ ጥቃቶችን በማክሸፍ ታሪክ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የ91ኛ ዓመቱ የምሥረታ በዓልም "በድል እና በመስዋዕትነት የደመቀ የኢትዮጵያ ሰማይ አለኝታ" በሚል መሪ ቃል ኅዳር 20 እና 21 ቀን 2019 ዓ.ም የሚከበር መሆኑን ተናግረዋል።
ኅዳር 20 በቢሾፍቱ ከተማ በርካታ ኢንተርናሽናል አትሌቶች የሚሳተፉበት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ "አየር ኃይላችን መመኪያችን" በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: