የኢትዮጵያ ርዕይ በሚያስብ አእምሮ እና በሚሠሩ እጆች ሲመራ ይሰምራል፣ ይጸናልም ሲሉ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።
ፕሬዚዳንት ታየ በመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸው፣ “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በድጋሚ በመመረጥዎ የተሰማኝን ደስታ ልገልፅ እወዳለሁ” ብለዋል።
ታሪካዊቷ ሀገር ኢትዮጵያን ያገለግሉ ዘንድ የተሳካና ፍሬያማ የሥራ ዘመን እንዲሆንልዎ ከልብ እመኛለሁም ብለዋል ፕሬዚዳንቱ በኤክስ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባጋሩት መልዕክት።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: