1. መከላከልን እና የአየር ንብረትን ማዕከል ያደረገ የጤና ፖሊሲ
✍🏽የሕዝብ ጤና የሚጀምረው ታማሚው ክሊኒክ ሲደርስ ሳይሆን፤ ንጹሕ ውኃ፣ የተመጣጠነ ምግብ እና ለሕፃናት ምቹ የመኖሪያ አካባቢን በማመቻቸት ነው።
✍🏽የዝናብና የሙቀት መጠን መለዋወጥ ለበሽታዎች መስፋፋት ምክንያት ስለሚሆን፣ ጤናን የልማት እና የኢንቨስትመንት ፖሊሲዎች ማዕከል ማድረግ ይገባል።
✍🏽ኢትዮጵያ በመጪው ዓመት በአዲስ አበባ በምታስተናግደው የዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ጉባኤ (COP32) ላይ የጤና ባለሙያዎች በሳይንሳዊ መረጃና ልምዳቸው በውሳኔ አሰጣጡ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
2. ማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እና የፋይናንስ ራስን መቻል
✍🏽በኢትዮጵያ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች መሠረታዊ የጤና አገልግሎትን ለቤተሰብ ተደራሽ ማድረግ ችለዋል።
✍🏽ዜጎች በሕመም ምክንያት ለከፍተኛ ወጪ እና ድህነት እንዳይዳረጉ የጤና መድን ሽፋን እየሰፋ ይገኛል።
✍🏽የውጭ የገንዘብ ድጋፍ ቢቋረጥ እንኳን የታካሚዎች ሕክምና እንዳይስተጓጎል፣ መንግሥታት በራሳቸው በጀት የጤና ተቋማትን፣ ላቦራቶሪዎችን እና የመድኃኒት አቅርቦትን በዘላቂነት መደገፍ አለባቸው።
3. የመድኃኒት ምርት እና የአኅጉራዊ ገበያ ትሥሥር
✍🏽ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ፓርኮቿ የመድኃኒት ምርትን እያሳደገች ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ያገኘችው የደረጃ 3 (Maturity Level 3) ዕውቅና ለሀገር ውስጥ እና ለቀጣናው ገበያ ጥራት ያለው መድኃኒት ለማቅረብ ትልቅ መሠረት ሆኗል።
✍🏽አፍሪካውያን መድኃኒቶችን እና የሕክምና ግብዓቶችን በጋራ በመግዛት ለአኅጉሪቱ አምራቾች አስተማማኝ ገበያ መፍጠርና ምርታማነታቸውን ማበረታታት ይኖርባቸዋል።
✍🏽አፍሪካውያን ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ሩቅ ሀገራት የሚያደርጉትን ጉዞ ለማስቀረት፣ በአኅጉሪቱ ውስጥ ደረጃቸውን የጠበቁ የሕክምና የልህቀት ማዕከላትን ማስፋፋት ያስፈልጋል።
4. ዲጂታል ጤና እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI)
✍🏽በገጠር ያለች አዋላጅ ነርስ ችግር ሲያጋጥማት በቀጥታ ከስፔሻሊስት ሐኪም ጋር መመካከር የምትችልበት እንዲሁም የታካሚዎች የሕክምና መረጃ ከአንዱ ተቋም ወደ ሌላው በደኅንነት የሚተላለፍበት ሥርዓት መዘርጋት አለበት።
✍🏽ሰው ሠራሽ አስተውሎት በአፍሪካውያን ተመራማሪዎች ተፈትኖ፣ በአፍሪካ ቋንቋዎች እና ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ተመሥርቶ መዘጋጀት አለበት፤ የመረጃ ደኅንነትም በራሳችን ሕግ መጠበቅ ይኖርበታል።
✍🏽የኢትዮጵያ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት እና አዲስ የተቋቋመው "የመደመር ሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ" ከመላው አፍሪካ ለሚመጡ ተማሪዎች እና ተመራማሪዎች የምርምርና የሥልጠና ዕድል ይከፍታሉ።
5. ተጠያቂነት እና ዓለም አቀፍ አጋርነት
✍🏽ለሚገቡ ቃል-ኪዳኖች ኃላፊነት የሚወስድ አካል፣ የፋይናንስ ምንጭ እና የግምገማ ጊዜ በግልጽ መቀመጥ አለበት፤ ስኬትም በወረቀት ሳይሆን በሕዝቡ የዕለት ተዕለት የሕክምና አገልግሎት መሻሻል መለካት ይኖርበታል።
✍🏽ዓለም አቀፍ አጋሮች ድጋፋቸውን ከአፍሪካ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር እንዲያጣጥሙ እና ዘላቂ የሀገር ውስጥ ተቋማትን በመገንባት ላይ እንዲያተኩሩ ጥሪ ቀርቧል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: