ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች፣ ታሸንፋለች፣ የጠላት ሴራን በጣጥሳ መሻቷን በተግባር ትከውናለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያ ከፊቷ የተደቀኑ ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎችን እንዲሁም የጠላቶቿን ሴራ በመሻገር የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ በስኬት እንደምትከውን ተናግረዋል።
ሀገራችን በታሪኳ አያሌ ፈተናዎችን አልፋ እዚህ የደረሰች በመሆኗ፣ አሁንም የጥፋት ኃይሎች የሚጋርጡባትን ሴራ በጽናት በመመከት መሻቷንና ዓላማዋን ከግብ ታደርሳለች ብለዋል።
በኢትዮጵያ ላይ የሚጎነጎኑ የጠላት ሴራዎች ሁሉ በሕዝቦቿ አንድነትና ጽናት እንደሚመክኑና ሀገራችን የጀመረችውን የልማት ግስጋሴ ማስቆም እንደማይችሉም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ምንጊዜም አሸናፊ ሆና እንደምትቀጥልና የሰነቀችውን የሁለንተናዊ ብልጽግና ታላቅ ርዕይም በወሬ ሳይሆን በጠንካራ ሥራ ወደ ተጨባጭ ውጤት ቀይራ ለዓለም እንደምታሳይ አረጋግጠዋል።
በሜሮን ንብረት
#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: