የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ያስገነባው የኢትዮጵያ ሚዲያ የልህቀት ማዕከል የምርቃት ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው።
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን አመራር አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ማዕከሉ የጋዜጠኝነት እና የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ አቅምን ለማጎልበት ያለመ ሲሆን የጋዜጠኞችን እና የመገናኛ ብዙሃን አመራሮችን እውቀት፣ ክህሎት እና የሥነ-ምግባር ደረጃ ማሻሻል ከተቋቋመባቸው ዓላማዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ዘርፉን በጥናት እና በስልጠና መደገፍ እንዲሁም የሚዲያ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን የሚያሳድጉ ስልጠናዎችን ተደራሽ ማድረግም የማዕከሉ ሌላው ዓላማ ነው።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የታደሙ እንግዶች ማዕከሉን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: