የዲፕሎማሲ ማዕከልና የአፍሪካ ሕብረት መዲና በሆነችው አዲስ አበባ አህጉራዊ አጀንዳዎችን በታላቅ ድምቀት የሚመራው ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ከደቂቃዎች በኋላ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሊጀምር ነው።
ለእድገት ማስተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ ኢኮኖሚያዊ መፃኢ እድል ነዳፊዎች በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ የሀገር መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በአዲስ አበባ ተገኝተዋል።
በጉባኤው ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከተለመደው የሥልጣን ሽሚያ ወጥተው፣ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ እና የዲጂታል ልማት መሪዎች በመሆን አህጉራዊ ትራንስፎርሜሽኑን ማፋጠን የሚችሉበት አዲስ ፍሬሚንግ እና የፖሊሲ አቅጣጫ ይመከራል ተብሎ ይጠበቃል።
በአስተናጋጅነት በኩል ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ያስመዘገበቻቸው ሰው ተኮር የልማት ስኬቶች ለአህጉሪቱ ተሞክሮ ሆኖ የሚቀርብበት ታሪካዊ መድረክ መሆኑ ተገልጿል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: