Search

ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ወታደራዊ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ

ረቡዕ ጥቅምት 25, 2019 49

የመከላከያ ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ ከውጭ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር የሚያደርጉትን ተከታታይ የወታደራዊ ዲፕሎማሲ ውይይት በመቀጠል በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክን ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

በውይይቱም ሁለቱ ሀገራት ዘመናት የተሻገረውን ታሪካዊ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማሳደግ እና በወታደራዊና ስትራቴጂያዊ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል።

አቶ መሐመድ እድሪስ በውይይቱ ወቅት፣ ፈረንሳይ አሁናዊ እና ስትራቴጂያዊ ወታደራዊ አቅምን ለማሳደግ እያደረገች ላለችው የእውቀት ሽግግር እና የሰላም ማስከበር ተቋማዊ አቅም ለማጠናከር እያደረገች ላለው ድጋፍ አመስግነዋል።

ኢትዮጵያ በቀጣናው ፍትሃዊ እና ህጋዊ ጥቅሟን ለማስከበር ለምታደርገው ጥረት ፈረንሳይ ከጎኗ እንድትቆምም ጠይቀዋል።

በትግራይ ክልል እየተከናወነ ያለውን የመልሶ ማቋቋምና የሠራዊት ማዋሃድ (DDR) ሂደት በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ሚኒስትሩ፣ ፈረንሳይ ለሂደቱ ስኬታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ በበኩላቸው፣ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነትና ሁለገብ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።

በተለይም በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በሚደረጉ ጥረቶች እንዲሁም በወታደራዊ ሥልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፎች የሚከናወኑ የጋራ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: