Search

ዲፕሎማቶችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በትግራይ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎች የተሀድሶ ማዕከልን ጎበኙ

ሓሙስ ጥቅምት 26, 2019 73

በኢትዮጵያ የሚገኙ የልዩ ልዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካዮች በትግራይ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎች ተሀድሶና መልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል በመገኘት የሥራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅት 5 ሺህ 500 የቀድሞ ታጣቂዎችን ተቀብሎ የተሀድሶ ስልጠና እየሰጠ የሚገኘው የመቐለው ማዕከል፣ ቀደም ሲልም በተመሳሳይ መልኩ ተገልጋዮችን ሲያስተናግድ መቆየቱ ተጠቅሷል።

በማዕከሉ የሚሰጠው ይህ ስልጠና የቀድሞ ታጣቂዎች ሰላማዊ ሕይወታቸውን እንዲመሩና ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ከማስቻሉም በላይ፣ ሀገራዊ የሰላም ግንባታው መስመር እንዲይዝ አዎንታዊ ድርሻ እያበረከተ ይገኛል።

በጉብኝቱ የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁንን ጨምሮ የኮሚሽኑ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

 

በአስማረ ብርሃኑ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: