Search

በሴራና በተንኮል የባህር በር እንድናጣ መደረጉ ሀገራችንን ለተለያዩ ተግዳሮቶች ዳርጓታል፦ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ

ቅዳሜ ጥቅምት 28, 2019 58

የቀድሞው የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎችና የፖሊስ ሠራዊት ማህበራት ህብረት አራተኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በጉባኤው ላይ በክብር እንግድነት በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ባህር ኃይል አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ሌላ ሀገርን ለመውረር ያለመ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ሕግና በዲፕሎማሲ አማካኝነት መፍትሔ ለማግኘት የሚደረግ ጥረት መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር መራቋ  ከታሪካዊ ስብራቶች አንዱ መሆኑን ያብራሩት ቫይስ አድሚራል ክንዱ በሴራና በተንኮል የባህር ኃይላችን እንዲፈርስ ብሎም የባህር በር እንድናጣ መደረጉ ሀገራችንን ለተለያዩ ተግዳሮቶች እንደዳረጋት አስረድተዋል።

ሀገራችን ከቀይ ባህር ጋር ያላት ታሪካዊ ትስስር ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ብቻ የተጀመረ አለመሆኑን የጠቆሙት አዛዡ አሰብና ምጽዋን ጨምሮ ከቀይ ባህር ጋር የነበራት የንግድ ግንኙነት ከጥንታዊ ሥልጣኔ ዘመን ጀምሮ የሚዘልቅ መሆኑን አሳስበዋል።

ተሰብሳቢዎቹ ሙሉ የሕይወት ዘመናቸውን በውትድርና አገልግሎት ያሳለፉ በመሆናቸው ያካበቱት ልምድና ያሳረፉት ታሪካዊ አሻራ ለአሁኑና ለቀጣዩ ትውልድ የሚጠቅም መሆኑን ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገልጸዋል።

 

ጠቅላላ ጉባኤው በቀድሞውና በአሁኑ የኢትዮጵያ ጦር ኃይል መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር የተሞክሮ ልውውጥ ለማድረግና የቀድሞ የጦር ኃይሎች አባላትን አስተዋጽኦ ለማስቀጠል ወሳኝ መድረክ መሆኑን ከመከላከያ ሠራዊት ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: