Search

ሕገወጡ የህወሓት ቡድን በክልሉ የፖሊስ ሠራዊቱን ለማፍረስ ያደረገው ሙከራ አልተሳካለትም፡- የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር)

ሓሙስ ኅዳር 03, 2019 112
በትግራይ ክልል የባለአደራ አስተዳደር የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) አስተዳደሩ የፖሊስ ተቋምን አጠናክሮ በተሻለ ደረጃ የሕዝብ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን ገለጹ።
የመቐለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከከተማዋ ፖሊስ አባላት ጋር በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ላይ ውይይት እያደረገ ይገኛል።
በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) የፖሊስ ተቋም ከየትኛውም ተቋም በላይ የማኅረሰቡን ችግር በቅርበት የሚያውቅና ለሕዝብ ከፍተኛ ውግንና ያለው መሆኑን አንስተዋል።
የፖሊስ አባላት እና አመራሮች በመድረኩ ተገኝተው የሕዝባቸውን ደኅንነት ለማስጠበቅ ላሳዩት ዝግጁነት እና ተነሳሽነትም አድንቀዋል።
በመቐለ ከተማ የሚጀመር መልካም ተሞክሮ ለሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ጥሩ አርዓያ እንደሚሆን አንስተው፣ ሕገወጡ የህወሓት ቡድን የፖሊስ ሠራዊቱን በክልሉ ለማፍረስ ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት ተናግረዋል።
በአስማረ ብርሃኑ
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: