Search

በዳካር 2026 የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቋ የሚያኮራ ታሪካዊ ውጤት ነው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሓሙስ ኅዳር 03, 2019 78

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዳካር 2026 የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ 5 የወርቅና 3 የብር በድምሩ 8 ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቋ የሚያኮራ ታሪካዊ ውጤት መሆኑን ገለጹ።

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ለዚህ ውጤት የበቃችሁ ወጣት አትሌቶቻችንን፣ አሰልጣኞቻችንንና የስፖርቱን ቤተሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ ብለዋል።

በስፖርት ዘርፍ በተለይም ዘመናዊና ተደራሽ የስፖርት መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት፣ የታዳጊ ወጣቶችን ተሰጥኦ በማውጣትና በማብቃት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮች የነበራትን ከፍተኛ ቦታ ዳግም እንድትይዝ የተጀመረው ሥራ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

 

 

የዛሬዎቹ ድሎች የነገዋ ታላቅ ኢትዮጵያ መሠረቶች መሆናቸውንም አመላክተዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: