ሳይንቲስቶች በሞሮኮ አትላስ ተራሮች ላይ አዲስ የዳይኖሰር ዝርያ አግኝተዋል።
ዳይኖሰሩ ከ165 ሚሊዮን ዓመታት በፊት የኖረ ሲሆን፤ ረዣዥም እና ሹል ቀንዶች በመላ ሰውነቱ ላይ ነበረው ተብሏል።
ከተመራማሪዎቹ አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቻርድ በትለር እንደገለፁት፤ ይህ ግኝት ለምርምር እጅግ በጣም ጠቃሚ እና ያልተለመደ ግኝት ያደርገዋል ብለዋል።
ሳይንቲስቶች እንደሚሉት፤ በተለይ በጭራው ላይ ያለው ሹል እና ረጃጅም ቀንድ፣ ዳይኖሰርቶች በአንድ ወቅት ጭራቸውን እንደ መሳሪያ ይጠቀሙበት እንደነበር ያመላክታል።
“ስፒኮሜለስ” የተሰኘው ይህ ዳይኖሰር ዝርያ 13 ጫማ ርዝመት ያለው እና 1-2 ቶን የሚመዝን እንደነበር ተገልጿል።
ዳይኖሰሩ ባለአራት እግር ሆነው ቀስ ብለው ከሚንቀሳቀሱ እና እፅዋትን ከሚመገቡ ዳይኖሰሮች መካከል አንዱ ነው ተብሏል።
በሴራን ታደሰ
#EBC #EBCdotstream #DinosaurDiscovery #ScienceNews