Search

12ቱ የዓድዋ ጦር ጄኔራሎች፡ የአንድነት እና የነጻነት ችቦ አብሪዎች

ቅዳሜ የካቲት 21, 2018 519

የዓድዋ ድል የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት እና ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ መሆኑን ዓለም ይመሰክራል። በወቅቱ የአውሮፓ ወራሪዎች አፍሪካን ለመቀራመት እንደተነሱት ሁሉ፣ የኢጣሊያ ወራሪ ኃይልም ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት ባሕር አቋርጦና ድንበር ጥሶ መጣ።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት መላው ሕዝብእምቢኝ ለሀገሬ! እምቢኝ ለኢትዮጵያ!” በማለት ኑሮውን፣ ትዳሩንና ልጆቹን ትቶ ወደ ዓድዋ ዘመተ።

ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ከወራሪው ጋር ሲነጻጸር እጅግ ኋላ ቀር መሣሪያ ቢታጠቁም፣ ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅርና ለራሳቸው የሚሰጡት ክብር ዘመናዊ መሣሪያ የታጠቀውን ኃይል እንዲያሸንፉ ስንቅ ሆናቸው።

ጠላትንም ድል ነሡ! እዚህ ላይ ታዲያ፣ ያላሰለሰ ጥበብና ጀግንነት የታከለበት አመራር በመስጠት ደማቅ ታሪክ የጻፉትን 12ቱን የጦር ጄኔራሎች ታሪክ ማንሣት ግድ ይላል።

ጀግኖቹ  12 የጦር መሪዎች እነማን ናቸው?

እነዚህ ጄኔራሎች ከየአካባቢው ተውጣጥተው በአንድ ዓላማ የቆሙ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው፦

ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ - (አባ ጎራው)

ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል - (አባ ቃኘው) [1844-1898] 

ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ተሰማ - (አባ ጠና) [1842-1893] 

ንጉሥ ሚካኤል አሊ ሊበን - (አባ ሸንቆ) [1840/43-1911]

ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮባ - (አባ ነፍሶ) [1854-1929]

ራስ ወሌ ብጡል ኃይለማርያም - (አባ ጠጣው) [1835-1910]

ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲንግዴ - (አባ መቻል) [1846-1919] 

ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ - (አባ ነጋ) [1840-1891] 

ራስ መንገሻ ዮሐንስ ምርጫ - (አባ ግጠም) [1857-1898] 

ዋግሹም ጓንጉል ብሩ /መድኅን - (አባ መርከብ

ራስ አባተ ቧያለው ንጉሡ - (አባ ይትረፍ) [1861-1910]

ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም - (አባ ገድብ)

የድሉ ፋይዳ እና ለዛሬው ትውልድ ያለው ትምህርት

እነዚህ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተውጣጡ መሪዎች በአርበኝነት እና በጀግንነት ተሰልፈው፣ በመላው ጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ የድል ፋና ወጊ የሆነውን የዓድዋን ድል አጎናፅፈውናል። በዓለም መድረክም ለጥቁር ሕዝቦች አዲስ ክብርና አመለካከት ፈጥረዋል።

ታላቅ አርበኝነታቸው፣ በከፍተኛ ኃላፊነት በአንድነት መሰለፋቸውና ብልህነት የተሞላበት የጦር አመራር ክህሎታቸው በቅኝ ገዢዎች ፊት በአሸናፊነት እንዲቆሙ አስችሏቸዋል። የመሪዎቹ ጀግንነት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ባለፈ፣ በአፍሪካና በመላው ዓለም ለሚገኙ ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት መነቃቃትን ፈጥሯል።

ዛሬም ቢሆን፤ አባቶቻችን ልዩነቶቻቸውን አቻችለው በአንድነት ጠላትን ድል እንዳደረጉት ሁሉ፣ የዛሬው ትውልድም ይህን የዓድዋን መንፈስ በመላበስ ሀገሩን ከድህነትና ከውጭ ጥገኝነት የማላቀቅ ታሪካዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።