ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ለሚኖሩ የተለያዩ ሀገራት ስደተኛ ቤተሰቦች የኢፍጣር መርኃ ግብር አከናውነዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ዛሬ ምሽት እንደተለመደው በረመዳን መንፈስ ከቡሩንዲ፣ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ከሶማሊያ፣ ከኢራቅ፣ ከሶሪያ፣ ከፍልስጤም፣ ከአፍጋኒስታን፣ ከኤርትራ፣ ከየመን እና ሱዳን ከመጡ ስደተኛ ቤተሰቦች ጋር አፍጥር ታድመናል ብለዋል።
#Ethiopia #Iftar #AbiyAhmed #Ramadan2026 #RefugeesInEthiopia