Search

የአፍሪካ አንድነት ቀንዲል - ኩዋሜ ኑኩሩማህ

እሑድ የካቲት 08, 2018 39

“ስንከፋፈል ደካሞች ነን፤ በአንድነት ከቆምን ግን አፍሪካ በዓለም ላይ ካሉ ለበጎ ዓላማ ከተሰለፉ ታላላቅ ኃይሎች አንዷ ትሆናለች” በሚለው ዝነኛ ንግግራቸው ይታወቃሉ - ጋናዊው ኩዋሜ ኑኩሩማህ (ዶ/ር)።

ኑኩሩማህ በአሜሪካና በእንግሊዝ አቅንተው የከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለው በመመለስ፣ ጋናውያንን በማስተባበር የቅኝ ግዛት ቀንበርን አስወግደዋል። በውጤቱም እ.አ.አ በ1957 ጋና ነፃነቷን ስትቀዳጅ፣ እርሳቸውም የመጀመሪያው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆኑ።

"የጋና ነፃነት ከመላው አፍሪካ ነፃነት ጋር ካልተቆራኘ ትርጉም የለውም" ያሉት ኑኩሩማህ ፤ ራዕያቸው በጋና ብቻ አልተገደበም። "አፍሪካ አንድ መሆን አለባት" (Africa Must Unite) የሚለው መጽሐፋቸውና ተከታታይ ንግግሮቻቸው የአህጉሪቱን መሪዎች ለጋራ ዓላማ አስተባብረዋል።

በወቅቱ ከኢትዮጵያው መሪ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እና ከሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ጋር በመሆን፣ እ.አ.አ በ1963 በአዲስ አበባ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) እንዲመሠረት ታላቅ ታሪካዊ ሥራ ሠርተዋል።

ኩዋሜ ኑኩሩማህ (ዶ/ር) አፍሪካ የራሷ የሆነ አንድ የጋራ ጦር፣ አንድ የጋራ ገንዘብና አንድ ማዕከላዊ መንግሥት ሊኖራት ይገባል ብለው በጽኑ ያምኑ ነበር።

ኑኩሩማህ ለአህጉሪቱ ክብርና አንድነት ለከፈሉት መሥዋዕትነት መታሰቢያ ይሆን ዘንድ፣ በአዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት ግቢ ውስጥ ሐውልት ቆሞላቸዋል።  

በጌትነት ተስፋማርያም

#EthiopianBroadcastingCorporation #Ethiopia #Ghana #KwameNkrumah #PanAfricanism #AU