Search

ኢትዮጵያ በተገቢው መንገድ ያልተጠቀመችበት ባህላዊ ሕክምና?

ቅዳሜ ነሐሴ 24, 2017 50

የባህል ሕክምናን ከዘመናዊው ሕክምና ጋር ተመጋጋቢ በሆነ መልኩ ለማስኬድ ምን መሰራት ይኖርበታል? ሲል የቅዳሜ መልክ ኑሮ ዘይቤ ፕሮግራም እንግዶችን ጋብዞ አነጋግሯል፡፡

የባሕል ሕክምና ከእፅዋት፣ ከእንስሳት እና ከማዕድናት ከሚገኙ ተዋፅኦዎች የሚሰጥ መሆኑን የባህል ሕክምና አዋቂዎች ማሐበር የዲሲፕሊን ኮሚቴ አጣሪ መሪጌታ ሐዲስ ዘመን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ የባህል ሕክምናን በሚገባው ልክ ተጠቅማበታለች ማለት አስቸጋሪ ነው ይላሉ መሪጌታ ሐዲስ፡፡

የባሕል ሕክምና ከሌሎች ባዕድ አምልኮዎች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለውም ማኀበረሰቡ መረዳት እንዳለበት ይገልጻሉ።

በኢትዮጵያ የባሕል ሕክምናን ከዘመናዊው ሕክምና ጋር ተመጋጋቢ ሆነው እንዲሔዱ የአርማወር ሐንሰን  የምርምር ኢንስቲትዩት እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት ደግሞ፤ በአርማወር ሃንሰን የምርምር ተቋም የባሕል እና ዘመናዊ መድኃኒት ተመራማሪ ባዪ አከለ ናቸው።

የባህል ሕክምናቸውን በአግባቡ መጠቀም ከቻሉ እንደቻይና፣ደቡብ ኮሪያ፣ ታይላድ እንዲሁም ከደቡብ አፍሪካ እና ከጋና  አንፃር ስንተያይ ኢትዮጵያውያን በብዙ መመዘኛዎች ወደኋላ ቀርተናል ይላሉ።

ይህ ማሳያ ኢትጵያውያን ያለንን ሐብት እና እውቀት ተጠቅመን ወደፊት መጓዝ እንደሚጠበቅብን ያሳያል ሲሉ ያስረዳሉ።

ሙያውን በትክክል አውቀው የሚያገለግሉ የባሕላዊ ሕክምና ባለሙያዎች እንዳሉ ሁሉ ያለ እውቀታቸው ገንዘብ ለማግኘት ብቻ ታስቦ በድፍረት የሚሰሩ ሰዎች መኖራቸው ተናግረዋል፡፡

የባህል ሐኪሞች የሚጠቀሙባቸውን መድኃኒቶች ለኢንስቲትዩቱ  በማቅረብ የደህንነት ሁኔታቸውን በጥናት የሚረጋገጥበት አሰራር መኖሩንም ተናግረዋል፡፡

ይህም ጥናት መድኃኒቱን በሚጠቀመው ሰው ላይ ጉዳት አለማድረሱን ለማረጋገጥ እንደሚጠቅም ገልፀዋል፡፡

ማኀበረሰቡ የባህላዊ ሕክምናን በሚጠቀምበት ወቅት ባለሙያዎቹ በቂ ዕውቀት እና ሙያ እንዳላቸው ማረጋገጥ ይኖርበታል ሲሉም አስረድተዋል።

 

በንፍታሌም እንግዳወርቅ

 #Ebc #ebcdotstream# #traditional #medicine