Search

የልብ ችግሮችን በሰከንዶች ውስጥ የሚለየው በሰውሰራሽ አስተውሎት የታገዘው የልብ ማዳመጫ

እሑድ ነሐሴ 25, 2017 49

በሰውሰራሽ አስተውሎት የታገዘ የልብ ማዳመጫ (ስቴቶስኮፕ) በሴኮንዶች ውስጥ ሶስት የተለያዩ የልብ በሽታዎችን ለመለየት ይረዳል ብለዋል ተመራማሪዎች።

የብሪታንያ ተመራማሪዎች ቡድን ዘመናዊ ስሪቱን በመጠቀም ጥናት ያካሄደ ሲሆን መሳሪያው የልብ ድካምን፣ የልብ ቫልቭ በሽታን እና ያልተለመዱ የልብ ምቶችን በቅጽበት እንደሚለይ አረጋግጠዋል።

መሳሪያው የልብ ድምፆችን እና ሪትሞችን በመመዝገብ፣ በሰውሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ ውጤቱን ይተነትናል ተብሏል።

በለንደን ውስጥ 12 ሺህ በላይ ታካሚዎችን ባሳተፈ ጥናት፣ ይህ በሰውሰራሽ አስተውሎት የታገዘ የልብ ማዳመጫ ከመደበኛው የበለጠ ውጤታማ መሆኑም ተረጋግጧል።

ዶክተሮች እንደሚሉት ይህ ግኝት የጨዋታ ቀያሪ ሊሆን ይችላል።

ይህም ታካሚዎች በድንገተኛ ህመም ሆስፒታል ውስጥ ሲደርሱ ብቻ ከመመርመር ይልቅ ቀደም ብለው እንዲታከሙ ያስችላቸዋል ነው የተባለው።

መሣሪያው ለንደን ውስጥ አስቀድሞ የተሞከረ ሲሆን በቅርቡ በደቡብ ለንደን፣ በሱሴክስ እና በዌልስ ሊሰራጭ ይችላል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሴራን ታደሰ

#EBC #EBCdotstream #stethoscope #healthcare