Search

ቻይና ለዓለም የመጀመሪያ የሆነውን 6G ቺፕ ይፋ አደረገች

እሑድ ነሐሴ 25, 2017 44

የቻይና ተመራማሪዎች በዓለም የመጀመሪያ የሆነውን የስድስተኛ ትውልድ (6G) ቺፕ ማምረት መቻላቸውን ዘገባዎች አመላከቱ።

ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ በገጠራማና ራቅ ባሉ አካባቢዎች የኢንተርኔት ፍጥነትን አሁን ካለው በ5 ሺህ እጥፍ ከፍ ማድረግ የሚችል ሲሆን፤ በገጠር እና በከተማ መካከል ያለውን የዲጂታል ክፍተት ለማጥበብ ትልቅ አቅም አለው ተብሏል።

በፔኪንግ ዩኒቨርሲቲ እና በሆንግ ኮንግ ሲቲ ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች የተሠራው ይህ “ሁሉን አቀፍ ድግግሞሽ” ቺፕ፣ በአንድ ሰከንድ ከ100 ጊጋቢት በላይ የሞባይል ኢንተርኔት ፍጥነት ማቅረብ የሚችል ሲሆን፤ ይህም መጠኑ 50 ጊጋባይት የሆነ ከፍተኛ ጥራት ያለው 8K ፊልም በሰከንዶች ውስጥ እንዲተላለፍ ያስችላል።

ይህ ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ጥቅሞች ቢኖሩትም ትችትም እየቀረበበት ነው። ተቺዎች ከጨመረው የኤሌክትሮማግኔቲክ ጨረር የሚመጡ የጤና አደጋዎች፣ ለሳይበር ጥቃቶች የመጋለጥ ዕድል መጨመር፣ የአካባቢ መራቆት እና ዲጂታል ክፍተትን ከማባባስ በተጨማሪ የግል መረጃዎች ክትትልና የግላዊነት ስጋትን ሊያባብስ እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ።

ተመራማሪዎቹ ቺፑን ወደ ስማርት ስልኮች፣ ድሮኖች እና ሌሎች መሳሪያዎች በቀላሉ ሊሰኩ በሚችሉ ሞጁሎች መልክ ለማስተካከል እየሠሩ መሆኑን ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል።

በሰለሞን ገዳ

#EBCdotstream #China #Internet #6G