Search

"ዜሌንስኪ ለሰላም ዝግጁ ከሆኑ ወደ ሞስኮ ይምጡ"፦ ፕሬዚዳንት ፑቲን

ረቡዕ ነሐሴ 28, 2017 49

የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬኑ አቻቸው ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ጋር በአካል ተገናኝተው ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ፑቲን ከዜሌንስኪ ጋር በአካል ተገናኝተው የሰላም ድርድር ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀው የዩክሬኑ አቻቸው ሞስኮን እንዲጎበኙ ጋብዘዋል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን በቤጂንግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በቅርቡ በአላስካ ባደረጉት ውይይት የባላንጣዎቹ ሀገራት መሪዎች በአካል ተገናኝተው መወያየት እንዳለባቸው መግባባት ላይ ደርሰው እንደነበር አንስተው፤ አሁን ለውይይቱ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

#EBCdotstream #Putin #Zelensky #Peacetalks #Moscow

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: