Search

ኢትዮጵያ እያመረተቻቸው ያሉ ድሮኖች ሉዓላዊነቷን በማስጠበቅ የተጀመረውን ብልጽግና ማስቀጠል የሚያስችሉ ናቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሓሙስ ነሐሴ 29, 2017 145

ኢትዮጵያ እያመረተቻቸው ያሉ ድሮኖች ሉዓላዊነቷንና ህልውናዋን በማስጠበቅ የተጀመረውን ብልጽግና ማስቀጠል የሚያስችሉ ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኤሮ አባይ የድሮን ማምረቻ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት፤ ኢትዮጵያ እያመረተቻቸው ያሉ ድሮኖች ሉዐላዊነቷን በማስጠበቅ የተጀመረውን ብልጽግና ማስቀጠል የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት በኢኮኖሚ ዕድገት ወታደራዊ አቅም በቅደም ተከተል  አብረው ማሳደግ ካልቻሉ ኢኮኖሚው በአቅም ማነስ ምክንያት ተመልሶ ሊበላ ይችላል ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂዎችን ከመግዛት አልፋ ማምረት መጀመሯ በዘርፉ አስደማሚና ተስፋ ሰጪ ውጤት እየተመዘገበ ስለመሆኑም ማሳያ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለመበልፀግ የሚያስችል ከፍተኛ አቅም ያላት ሀገር ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በግብርና፣ በቴክኖሎጂ፣ በቱሪዝም እና በማዕድን ዘርፎች ላይ እየመጣ ያለው ውጤት ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በሐይማኖት ከበደ