በቻይና በቾንግኪንግ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሙያ ትምህርት ኮሌጅ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ለመቀበል የተለያዩ ዘመናዊ መሣሪያዎች አገልግሎት ላይ ውለዋል።
ከእነዚህም መካከል፣ ሮቦቶች ተማሪዎችን በመምራትና ቀላል ጥያቄዎችን በመመለስ ሻንጣዎቻቸውን ሲያጓጉዙ ታይተዋል።
በአየር ላይ የሚበሩ ድሮኖች ደግሞ አቅጣጫ የሚጠቁሙ ማስታወቂያዎችን ያስተላልፉ የነበረ ሲሆን፣ ሻንጣዎችንም ወደ ተማሪዎች ማደሪያ ክፍሎች አድርሰዋል።
እንደ ሲሲቲቪ ኒውስ ዘገባ ትናንሽ ሮቦት ውሾች ቦርሳ በመያዝ እና ከአዲስ ተማሪዎች ጋር ፎቶ በመነሳት የብዙዎችን ቀልብ ስበዋል።
በሰለሞን ገዳ