Search

ውሃ-አልባ የልብስ ማጠቢያ ማሽን ለጠፈርተኞች

ዓርብ መስከረም 02, 2018 28

ቻይና ለጠፈርተኞች ተብሎ የተሰራ ውሃ-አልባ የልብስ ማጠቢያ ማሽን ይፋ አደረገች።

ይህ ፈጠራ የጠፈር ጉዞ ላይ የንጽህና ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ነው።

ጠፈር ላይ ውሃ ውስን በመሆኑና እና የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች ባለመኖራቸው ጠፈርተኞች ልብሳቸውን ደጋግመው ለመልበስ ይገደዳሉ።

የቻይና የጠፈርተኛ ምርምር እና ስልጠና ማዕከል ተመራማሪዎች የፈጠሩት አዲሱ ማሽን ለዚህ ችግር መፍትሄ ይዞ መጥቷል።

የአነስተኛ ሻንጣ መጠን ያለውና 12 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ይህ መሳሪያ ልብሶችን ለማፅዳት እንፋሎት፣ ኦዞን እና የአልትራቫዮሌት ጨረሮችን ይጠቀማል።

ማሽኑ በየዑደቱ 400 ሚሊ ሊትር ውሃ ብቻ ይፈልጋል። የጽዳት ሂደቱም 30 ደቂቃ ብቻ የሚወስድ ሲሆን፤ 99.9 በመቶ ቆሻሻን የማጽዳት አቅም አለው።

ይህ ውሃ-አልባ ማሽን በጠፈር ተልዕኮዎች ወቅት የሚያስፈልገውን የልብስ መጠን ከ60 በመቶ በላይ ሊቀንስ እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ይህ ደግሞ ጨረቃ እና ማርስን ወደመሳሰሉ አካላት ለሚደረጉ ረጃጅም ጉዞዎች ወሳኝ ጥቅም አለው ይላሉ።

ሳውዝ ቻይና ሞርኒግ ፖስት

በሰለሞን ገዳ

#china #space #laundry #washingmachine #astronauts