ዩካን (you can) የተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ ከሆቴሎች፣ ከድርጅቶች፣ ከመኖሪያ ቤቶች የተውጣጡ ቆሻሻዎችን ለገዢዎች የሚያገበያይ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ጥቅሙም ጥፁህ እቃን ለማምረት እና ገንዘብን ለማግኘት ያግዛል፡፡
የተሰበሰበው ቆሻሻ በመመዘን በአፕልኬሽኑ ላይም መረጃውን ያሰፍራሉ፤ መተግበሪያውም ወደ ብርም ቀይሮ ምን ያህል ያወጣል የሚለውን ያስቀምጣል፡፡
መተግበሪያው 2 አይነት ጥቅም ያለው ሲሆን፤ ቆሻሻ ያላቸው ሰዎች መተግበሪያው ላይ መልዕክት በማስቀመጥ ቆሻሻው እንዲወሰድላቸው ያሳውቃሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ ቆሻሻ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚሰበስቡ ሰዎች መተግበሪያውን ጭነውት የት ቦታ ላይ የሚሰበሰብ ቆሻሻ እንዳለ ያመላክታቸዋል፡፡
ቆሻሻውን የሚሰበስቡት አካላት መተግበሪያው በሚመራቸው አቅጣጫ መሰረት በቀጥታ ቦታውን ማግኘት እንደሚችሉ ተመላክቷል።
መተግበሪያው ይህን ያህል ቆሻሻ ተዘጋጅቶልሃል፤ በማለት መልዕክት ለሚመለከተው ሰው እንዲደርስም ያደርጋል።
መተግበሪያው የቤት ቁጥርን ጨምሮ የግለሰቡን አድራሻ ስለሚመዘግብ ቦታውን ለማወቅ እንዳይቸገሩ ይረዳል፡፡
ቆሻሻ ብር ነው የሚለው የቴክኖጂው ባለቤት የሆነው ተቋም፤ መተግበሪያውን ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ መዋሉን አሳውቋል።
በመተግበሪያው አማካኝነት የሚሰበሰበው ቆሻሻም ለባዮጋዝ እና ለባዮፈርትላይዘርነትም እያገለገለ መሆኑ ተመላክቷል።
ለጽዱ እና አረንጓዴ ሀገርም ሰፊ ሚና እንደሚጫወት እየተነገረ ይገኛል፡፡
በሜሮን ንብረት
#EBC #ebcdotstream #Clean #Tech