በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ጉዞ የተመዘገቡ ውጤቶች ለቀጣዩ ሥራ መደላድል የፈጠሩ መሆናቸውን በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይሲቲ መሠረተ ልማት ግንባታ እና አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ ኃይሉ ይገልጻሉ።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ከመቀረፁ በፊት የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 17 ሚሊየን የነበረ ሲሆን፤ ስትራቴጂው ከተተገበረ በኋላ ቁጥሩ ወደ 55 ሚሊዮን ማደጉን አንስተዋል።
በኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂው መስፋፋት በተለያዩ የኢኮኖሚ አውታሮች ላይ ውጤቶች እያስገኘ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በማኅበራዊ አገልግሎት፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂው፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርናው እና በተለያዩ ዘርፎች የተገኙ ለውጦች የዲጂታል 2025 ትሩፋት ናቸው ሲሉ አስረድተዋል።
ከኢኮኖሚው ባሻገር ከሉአላዊነት እና ከማንነት ጋር ተያይዞ ቴክኖሎጂው ወሳኝ በመሆኑ በትኩረት እየተሰራበት እንደሆነ ገልፀዋል።
በቀጣይ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ በአራት ጉዳዮች ላይ በትኩረት የሚሰራ ሲሆን፤ በዋናነት አካታች የሆነ የተቀናጀ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
በሔለን ተስፋዬ
#EBC #ebcdotstream #DigitalEthiopia