Search

6 ተሳፋሪዎችን የሚይዙት የኤሌክትሪክ የአየር ላይ ታክሲዎች

ማክሰኞ መስከረም 13, 2018 82

በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የአየር ላይ ታክሲዎች አቅም ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ ይገኛል።
ሁለት እና አራት ተሳፋሪዎችን የሚይዙ የአየር ላይ ታክሲዎች በተለያዩ ዓለማት እየተሞከሩ ነው።
በእንግሊዝ ብሪስቶል የሚገኘው ቨርቲካል ኤሮስፔስ የተሰኘው ተቋም 6 ተሳፋሪዎችን የሚይዙ እና 161 ኪሎ ሜትር መብረር የሚችሉ 25 የኤሌክትሪክ የበረራ ታክሲዎችን በአንድ ዓመት ውስጥ ሊያመርት መሆኑን ገልጿል።
ኩባንያው እ.አ.አ በ2035 ላይ 900 የበረራ ታክሲዎችን እና ለአየር በረራው የሚያስፈልጉ ባትሪዎችን በየዓመቱ ለማምረት መወጠኑን የዘገበው ቢቢሲ ነው።
 
በሴራን ታደሰ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: