Search

ጣና ሐይቅና በዙሪያው ያሉ ደሴቶችን በባህላዊና ተፈጥሯዊ የዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተሰራ ነው

ረቡዕ መስከረም 14, 2018 129

ጣና ሐይቅ እና በዙሪያው ያሉ ደሴቶችን በባህላዊና ተፈጥሯዊ የዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው ጣና ሐይቅን ከገዳማቱና አዋሳኝ ውኃ አዘል መልከዓ-ምድር ጋር አካቶ በባህላዊና ተፈጥሯዊ የአለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እየሠራ መሆኑን ነው የገለፀው።

ጣና ሐይቅና በዙሪያው ያሉ ደሴቶች የያዟቸውን የባህልና የተፈጥሮ መካነ-ቅርሶችን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የተጀመሩ ስራዎች ውጤት ማስገኘታቸው ተገልጿል።

የጥናት ስራው በመከናወን ላይ የሚገኘው ቅርሱ፤ በያዝነው ዓመት ማገባደጃ ላይ በኮሪያ ሪፐብሊክ ቡሳን ከተማ በሚካሄደው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ 48 መደበኛ ጉባኤ ላይ የምዝገባ ማረጋገጫ እንደሚያገኝ ይጠበቃል።

በጣና ሐይቅ ውስጥ በቋጥኝ እና በደን የተሸፈኑ ከ37 በላይ ደሴቶች የሚገኙ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥም አብዛኞቹ ታሪካዊ ገዳማትን እና አድባራትን ይዘዋል፡፡

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #LakeTana #UNESCO