የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡና ለተጎዱ ዜጎች የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክት፣ለኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ፕሬዝዳንቱ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦችና በጉዳቱ ለተጎዱ ወገኖች ሁሉ ያላቸውን ጥልቅ ስሜትና አጋርነት ገልጸዋል።
ሶማሊያ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን በጽናት እንደምትቆምም ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ አረጋግጠዋል።
#EthiopianBroadcastingCorporation #Ethiopia #Somalia #Solidarity #Landslide