የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ እና ለተጎዱ ዜጎች የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገለጹ።
ፕሬዚዳንቱ ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በላኩት መልዕክት፣ በአደጋው ሳቢያ ለተጎዱ ወገኖች ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል።
በመሬት መንሸራተቱ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን የተመኙት ፕሬዚዳንት ፑቲን፣ አደጋው ያስከተለውን ጉዳት ተከትሎም የሩሲያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጎን መቆሙን አመላክተዋል።
በመሬት መንሸራተቱ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን የተመኙት ፕሬዚዳንት ፑቲን፣ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችም በፍጥነት እንዲያገግሙ ያላቸውን መልካም ምኞት አስተላልፈዋል።