በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውስጥ የሚገኙ ስታርታፖች ያላቸው አቅም እና ተነሳሽነት የሚደነቅ መሆኑን የጃፓን የኢኮኖሚ፣ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር (METI) የአፍሪካ ዋና ተወካይ ሀሺሞቶ ያሱሂሮ ገለጹ።
ሀሺሞቶ ያሱሂሮ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ሀሺሞቶ ያሱሂሮን እና ልዑካቸውን ተቀብለው ኢንስቲትዩቱ ስለሚሠራቸው ሥራዎች ገለጻ አድርገዋል።
በገለጻቸውም ኢንስቲትዩቱ የማኅበረሰብን ችግሮች ለመፍታት ከሚሠራው ሥራ በተጨማሪ ስታርታፖችን በመደገፍ እያከናወነ ስላላው ተግባራት እና በዩኒፖድ በኩል እተሰሩ ያሉ ሥራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የጃፓን የኢኮኖሚ፣ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአፍሪካ ዋና ተወካይ ሀሺሞቶ ያሱሂሮ በኢንስቲትዩቱ ውስጥ የሚገኙ ስታርታፖች ያላቸውን አቅም እና ተነሳሽነት አድንቀዋል።
ስታርታፖቹን ከዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ሥነ-ምኅዳር ጋር ለማገናኘት በሚቀጥሉት ዓመታት ወጣቶችን በዘርፉ ለማብቃት እና ለመደገፍ የሚያስችል ሥራ በጋራ እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።
ተወካዩ ጃፓን የኤ.አይ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት እና ለመደገፍ በትኩረት እንደምትሠራ ገልጸው፣ ወጣቶች ያላቸውን የኤ.አይ እውቀት ወደ ምርት እና አገልግሎት እንዲቀይሩት ድጋፍ ይደረጋል ማለታቸውን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የጃፓን መንግሥት በአፍሪካ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በቴክኖሎጂ ለመፍታት እና የአካባቢውን የፈጠራ ሥራዎች ለመደገፍ ሙሉ ቁርጠኝነት እንዳለው በዚሁ ወቅት ተመላክቷል።
#Ethiopia #Japan #AI #Africa #technology