Search

ችላ ሊባል የማይገባው ጤናማ አመጋገብ

እሑድ መስከረም 18, 2018 126

ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች በበዓል ወቅት መመገብ ለተለያዩ የጤና ችግሮች እንደሚያጋልጥ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ይገልፃሉ።
በተለይ በመስቀል በዓል ወቅትም ሆነ ከበዓሉ በኋላ ባሉት ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች ክትፎ፣ ጥሬ ስጋ እና የምግብ ቅቤ የበዛባቸውን የእንስሳት ተዋጽዖዎችን የመመገብ ልምዱ ከፍተኛ ነው።
ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች በብዛት መመገብ ስንጀምር የምግብ አለመፈጨት፣ የሆድ መንፋት፣ ማቃጠል፣ ቁርጠት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ እና መሰል ህመሞች እንደሚጀምሩ የስነ-ምግብ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
ሰውነታችን ወደ ውስጥ የገባውን ቅባት በሚፈልገው መጠን ከተጠቀመ በኋላ ቀሪው በስብ መልክ በብዛት ስለሚያከማችም ለተጓዳኝ በሽታ ያጋልጣል፡፡
እንደነዚህ ዓይነት ችግሮች እንዳይከሰቱ የተመጣጠነ የአመጋገብ ስርዓት አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዎች ያነሳሉ።
በ24 ሰዓታት ውስጥ ከሁሉም የምግብ ክፍሎች ማለትም ከጥራጥሬ፣ ከአትክልትና ፍራፍሬ ከእንስሳት ተዋጽኦ የተሰባጠረ ጤናማ አመጋገም ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የስነ-ምግብ ባለሙያዎች ይመክራሉ።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ:

ተያያዥ ዜናዎች: