Search

5ጂ ኢንተርኔት የሚጠቀመው የቻይና ትራክተር

ረቡዕ መስከረም 21, 2018 34

ቻይና ከአምስት ዓመታት በፊት በሙከራ ደረጃ የጀመረችውን ስማርት ትራክተር ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ አስገብታለች፡፡

ሀገሪቱ በግብርናው ዘርፍ እያደረገችው ባለው ምርምር ስማርት ግብርናን ተግባራዊ የሚያደርግ የላቀ የትራክተር ቴክኖሎጂን ይፋ ያደረገች ሲሆን፣ ራስ ገዝ የሆነው ኤሌክትሪክ ትራክተር ከፍተኛ የፈረስ ጉልበት ያለው እንደሆነ ተነግሯል።

"ሆንግሁ T70" የተባለው ይህ የቻይና የመጀመሪያው አሽከርካሪ አልባ ትራክተር፣ እንቅስቃሴውን በስልክ እና ኮምፒውተር በመቆጣጠር ብቻ ከዘር እስከ ሰብል ስብሰባ ያለውን ሙሉ የእርሻ ዑደት ራሱን ችሎ የሚያከናውን ነው።

በሊቲየም-አዮን ባትሪ የሚንቀሳቀስ መሆኑ ዓለምን እያሳሰበ የመጣውን የጋዝ ልቀት በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ ሲሆን፣ በአንድ ቻርጅ አስከ ስድስት ሰዓታት ሊሠራ እንደሚችል ተነግሮለታል።

የተገጠመለት የሰው ሠራሽ አስተውሎት የቁጥጥር ሥርዓት፣ 5 ኢንተርኔት እና የሳተላይት አሰሳ ሥርዓት ይህ ትራክተር የተሰማራበትን ሥራ በከፍተኛ ብቃት እና ያለምንም መዛነፍ እንደሚሠራ ተጠቅሷል።

በሥራ ላይ ሆኖ የአፈር ሁኔታ፣ የአየር ሁኔታ፣ የሰብል ጤና እና ሌሎች ቁልፍ የአግሮኖሚክ ሁኔታዎች ላይ ትክክለኛ መረጃን በመሰብሰብ የሚልክ ሲሆን፣ ይህም ለገበሬዎች እና ተመራማሪዎች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥን ያመቻቻል ተብሏል።

ትራክተሩ በተለያዩ የቻይና ግዛቶች ውስጥ ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሆነ "አግሮ ስፔክትረም" መረጃ አመልክቷል።

ይህ አርሶ ከመዝራት እስከ ሰብል እንክብካቤ እና አዝመራ መሰብሰብ ድረስ ያለውን አጠቃላይ የግብርና ዑደትን ይደግፋል የተባለለት ትራክተር፣ የግብርና ሥራዎችን ቅልጥፍና እና ጥራት በእጅጉ እንደሚያሳድግም ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

በለሚ ታደሰ

#EBC #ebcdotstream #smartagriculture #HonghuT70