የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ሥርጭት መጀመሩ ዜጎች በሀገሪቱ የሚወጡ ሕጎችን ተገንዝበው መብትና ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ እንደሚያስችል የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሱልጣን አብዱሰላም ተናገሩ፡፡
አፈ ጉባዔው፤ በኢትዮጵያ የፓርላማ ታሪክ እና እድሜ ረዥም እንደመሆኑ፣ የምክር ቤቶችን እንቅስቃሴ በተመለከተ መረጃዎችን ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ ረገድ ውስንነቶች እንደነበሩ አንስተዋል።
የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ስርጭት መጀመር ለዚህ ትልቅ መፍትሄ መሆኑን የገለጹት አፈ ጉባዔው፤ ዜጎች የሕግ አውጪው አካል የሚያከናውናቸውን ተግባራት በአግባቡ እንዲረዱ ያስችላል ነው ያሉት።
በተለይ ዜጎች በምክር ቤት የሚወጡ ሕጎችን ተገንዝበው መብታቸውን እንዲያስከብሩ እና ግዴታቸውን እንዲወጡ
ሙሉ መረጃ ሊኖራቸው እንደሚገባ ነው ያነሱት።
በዚህ ረገድ ኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ወቅቱን ያገናዘበ የመፍትሄ እርምጃ ስለመሆኑ ነው አፈ ጉባዔው የጠቆሙት።
በቴዎድሮስ ታደሰ