Search

ከአሰብ ደጃፍ ላይ ሆነው የባሕር በር የሚናፍቁት የሱልጣን አሊ ሚራህ ልጆች

ረቡዕ የካቲት 25, 2018 47

አፋሮች ከአባቶቻቸው የወረሱትን ኢትዮጵያዊነትና የቀይ ባሕር ባለቤትነት መንፈስ ይዘው፣ በሴራ ያጣነውን የባሕር በር በሰለጠነ ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለማስመለስ በጽናት እንደሚታገሉ አስታወቁ።

የአፋር ህዝብ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ትስስር ጥንታዊና የማይበጠስ መሆኑን የገለጹት የኤሊ ዳአር ወረዳ የሀገር ሽማግሌዎችና ነዋሪዎች፣ የቀይ ባሕር በር ለሀገር ህልውና ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

የሀገር ሽማግሌ አቶ መሐመድ አብደላ ከኤሊ ዳአር ወረዳ፣ "አፋርነት ከኢትዮጵያዊነት ጋር የተገመደ የጥንት ማንነት ነው። ሱልጣን አሊ ሚራህ አንፈሬ 'አፋር አፋር ነው፤ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ግመሎቹም የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ለይተው ያውቃሉ' ሲሉ የገለጹት ይኸው የማይበጠስ ትስስር ነው።

ሱልጣኑ ኢትዮጵያ የባሕር በሯን እንዳታጣ የከፈሉት ታላቅ መስዋዕትነት ዛሬም በትውልዱ ልብ ውስጥ ህያው ሆኖ ጥያቄው ሳይበርድ ይኖራል ብለዋል የወረዳው ነዋሪዎች።

ዛሬም ከአሰብ ደጅ ከኤሊ ዳአር ሆነን የምናውጀው አንድ እውነት አለ፤ ቀይ ባሕር ታሪካዊ አካል የሁላችንም ኩራት ነው በማለት ተናግረዋል፡፡

አፋር ያለ ኢትዮጵያ አይኖርም። ቀይ ባሕር የኛ ነው፣ እኛ የኢትዮጵያ ነን።" በማለት የአፋርን የማይነጣጠል የኢትዮጵያዊነት ትስስር ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የባሕር በርን ለማስመለስ ለምታደርገው ዲፕሎማሲያዊ ትግል የአፋር ህዝብ እንደሚደግፍ እና ለውጤት እንዲበቃ እንደሚሰራም አቶ መሐመድ አብደላ አረጋግጠዋል።

በላሉ ኢታላ

#Ethiopia #RedSea #HistoricalRight #Geopolitics #MaritimeLaw #NationalInterest #Africa