Search

ለ10 ዓመታት በአልጋ ላይ የቆየችው ሕፃን ብሌን አሸናፊ የ4 ሚሊዮን ብር ድጋፍና የመኖሪያ ቤት ተበረከተላት

ረቡዕ የካቲት 25, 2018 38

በከፍተኛ የአንጎል ውስጥ ውሃ መቋጠር እና የአንጎል ግፊት መጨመር (ሀይድሮሴፋለስ) ምክንያት ላለፉት 10 ዓመታት በአልጋ ላይ የቆየችው ሕፃን ብሌን አሸናፊ፣ ወደ ውጭ ሀገር ሄዳ ለምትታከምበት 4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገላት።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሕፃኗ መኖሪያ ቤት ተገኝተው ድጋፉን ለወላጅ አባቷ አስረክበዋል።

የሕፃን ብሌን አባት ወጣት አሸናፊ፣ በጽዳት ሠራተኝነት እየተገኘ እናት በሌሉበት ብሌንን፣ ታናሽ እህቷን፣ አካል ጉዳተኛ እህቱን እና አቅመ ደካማ እናቱን የሚንከባከብ ጠንካራ ወጣት መሆኑን ከንቲባዋ ገልጸዋል።

ቤተሰቡ በአሁኑ ወቅት የሚኖርበት ቤት ለሕፃኗ ጤና አስቸጋሪ በመሆኑ፣ አስተዳደሩ የተሻለ የመኖሪያ ቤት እንዲያገኙ መወሰኑንም አስታውቀዋል።

ለሕፃን ብሌን አጠቃላይ የሕክምና ወጪ የሚውለውን 4 ሚሊዮን ብር የሸፈኑት ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ መሆናቸውን የጠቀሱት ከንቲባ አዳነች፣ ለባለሀብቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልእክትም፤ ሕፃኗ አስፈላጊውን ሕክምና አግኝታ እንደ እኩዮቿ የምትቦርቅበትና ትምህርት ቤት የምትሄድበት ጊዜ ቅርብ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

#EBC #Ethiopia #AddisAbaba #AdanechAbiebie #HumanitarianSupport #HealthCare