7ኛው የታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና ሥነ-ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መእልክት፤ የ7ኛው የታማኝ ግብር ከፋይ እውቅና ሥነሥርዓት ተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ባለፈው ዓመት የምታዋጡት ግብር ለጋራ እድገትና ለሕዝባዊ ጠቀሜታ በሚውሉ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ እንደሚውል ቃል ገብተን ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬ በከተማችን ኮሪደሮች የሚታየው ለውጥ ለዚያ ቃላችን ሕያው ምስክር ሆኖ ይታያል ሲሉ ገልፀዋል።
የዛሬ ጥረታችሁ የነገን ትውልድ የተሻለ መፃኢ እድል እየቀረፀ ነው ሲሉም አመልክተዋል።
ሙስናን እና ሌብነትን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ሥርዓቶችን የማጠናከር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅሰዋል።
ግብር ከፋዮችም በመሰል ጎጂ ተግባር የተሠማሩ ሰዎችን ባለመተባበር እንዲያግዙ ያሳሰቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በጋራ ግልጽ፣ ተጠያቂነት የሰፈነባት እና የበለጸገች ሀገር እንገነባለን ብለዋል።