የመንግስት የመልማት ፍላጎት ሊሳካ የሚችለው በታማኝ ግብር ከፋዮች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 7ኛው የታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና እና ሽልማት መርኃ ግብር ተከናውኗል፡፡
በመርኃ ግብሩ ላይም ለ700 ታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ ባሰሙት ንግግር፤ ባለፈው ዓመት ስርዓት ለማበልፀግና ኢትዮጵያን ለማበልፀግ ቃል ገብተን ነበር፤ ሁለቱንም እያሳካን ነው ብለዋል፡፡
የመንግስት የመልማት ፍላጎት ሊሳካ የሚችለው በታማኝ ግብር ከፋዮች ነው ሲሉም ገልፀዋል፡፡
በ7ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና መርኃ ግብር 105ቱ የፕላቲኒየም፣ 245ቱ የወርቅ እና 350 የሚሆኑት ደግሞ የብር ተሸላሚዎች ሆነዋል፡፡
30 ተቋማት ባለፉት 4 ዓመታት የፕላቲኒም ደረጃ ተሸላሚ በመሆናቸው ልዩ ተሸላሚዎች በመሆን እውቅና አግኝተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ገቢንና የታክሰ ምጣኔን በየዓመቱ በ1 በመቶ ለማሳደግ የተያዘው አቅድ በ2017 አፈፃፀሙ ስኬታማ እንደነበር ተገልጿል፡፡
በአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማእከል በተካሄደው በዚህ መርኃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በተመስገን ሽፈራው
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #pmabiy #tax