Search

በታማኝ ግብር ከፋዮች ገንዘብ ሀገር እየተሠራች ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ረቡዕ መስከረም 28, 2018 126

በታማኝ ግብር ከፋዮች ገንዘብ ሀገር እየተሠራች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትላንት በተካሄደው 7ኛው የታማኝ ግብር ከፋይ ዕውቅና እና ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር፤ ያለ ማንም እገዛ እና ብድር በግብር ከፋዮች ገንዘብ የቆሸሹ እና ምቹ ያልሆኑ ከተሞችን ለትውልድ በሚመጥን መልክ በመሥራት ማሳየት ችለናል ብለዋል።
አዲስ አበባን ተዘዋውሮ መጎብኘት ለዚህ ጥሩ ማሳያ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህም ታማኝ ግብር ከፋዮችን አመስግነዋል።
በእናንተ ታማኝ ግብር ከፋዮች ገንዘብ ሀገር እየተሠራች መሆኑን ዳግም በኩራት ልገልጽላችሁ እወዳለሁ ሲሉም አክለዋል።
በሜሮን ንብረት