ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመከራም ሆነ በስኬት ጊዜ በጋራ መቆም ይገባል ሲሉ በ7ኛው ታማኝ የግብር ከፋዮች የእውቅና እና ሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ ተናግረዋል፡፡
የኩባንያ ባለቤቶች እና የሥራ ኃላፊዎች ከትርፍ በላይ ማኅበራዊ ዓላማን ያነገበ ሥራ ማከናወን አንዱ እና ዋነኛ ተልዕኳቸው ሊሆን ይገባል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
ሥራ ሰርቶ ከግማሽ ቢልዮን ብር በላይ ግብር መክፈል የሚችል፣ ከትርፍ በላይ ለማኅበራዊ ዓላማ ራሱን ማዘጋጀት ይኖርበታል ነው ያሉት፡፡
በስኬትም ሆነ በተግዳሮት ጊዜ ከመንግስት እና ከሕዝብ ጋር ፀንቶ በመቆም ታማኝ መሆን እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
በንፍታሌም እንግዳወርቅ