የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ መደበኛ ስብሰባው ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን አዳምጧል።
የድጋፍ ሞሽኑን አስመልክቶ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር የተከበሩ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የመንግስት የተኩረት መስኮችን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡
ምክር ቤቱ በመጀመሪያ አጀንዳም በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለጉባኤን መርምሮ በማጽደቅ ስብሰባውን ጀምሯል።
ምክር ቤቱ ከዚህ በመቀጠልም ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን አዳምጧል።
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስትን የትኩረት ነጥቦችን አስመልክቶ ለህዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ የመክፈቻ ንግግር ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
በመስከረም ቸርነት
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #etvparlama #parlama