Search

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሀገራዊ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ ነው - ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ

ሓሙስ መስከረም 29, 2018 186

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ በመታጠቅና ብቁ ሰራዊት በማፍራት ሀገራዊ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ መሆኑን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ተናገሩ፡፡

በአየር ኃይል አካዳሚ መሠረታዊ ውትድርና ሙያ የሰለጠኑ ምልምል ወታደሮች የማስመረቅ ስነ ስርዓት ተካሄዷል።

በዚህም 230 መሰረታዊ ውትድርና ሙያ የሰለጠኑ ምልምል ወታደሮች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ለመኮንኖች የማዕረግ ሹመት የማልበስ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።

በዚህ ወቅት የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ እንደገለፁት አየር ኃይሉ ግዳጆችን በብቃት እየፈፀመ ይገኛል።

ሀገር እያከናወነች ያለው የልማት ስራ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወን እየተደረገ ነው ያሉት ሌ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ፤ የሰው ሀይል በማጠናከርና ዘመናዊ መሳሪያ በመታጠቅ ሰራዊቱ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ አየር ኃይል የመገንባት ውጥን ይዛ እየሰራች ነው ሲሉም ሌ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ ገልጸዋል።

በአባዲ ወይናይ

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #AirForce