Search

አርሶ አደሩ ያለውን ሐብት የሚያሰማራበትን መንገድ መምራት ያስፈልጋል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

ሓሙስ መስከረም 29, 2018 111

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ "የጋራ ዲጂታል ነጋችንን ለማሳደግ ኢትዮጵያ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ናት" ሲሉ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በናይሮቢ፣ ኬንያ “ዲጂታላይዜሽንን ለቀጠናዊ የእሴት ሰንሰለት መጎልበት በመጠቀም ለዘላቂ እና አካታች እድገት ማዋል” በሚል ጭብጥ በተካሄደው 24ኛው የCOMESA መሪዎች ጉባኤ ላይ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የአፍሪካን የኢኮኖሚ ታሪክ የመቀየር ልዩ ዕድል እንዳቀረበ አፅንኦት ሰጥተው ማንሣታቸውን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
እንደ አኅጉር የየሀገሮቻችንን ጥረቶች ለማጣመር እና ቀጠናዊ ትሥሥሮችን ለማፋጠን ክሂሎቱ እና መሠረቱ አለን ሲሉም አመላክተዋል።
በኢትዮጵያ ዲጂታል ክሂሎትን ለማበልጸግ እና አስፈላጊ መሠረተ ልማት ለመገንባት ጥሩ ርምጃዎች ተራምደናል በማለት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ የጋራ ዲጂታል ነጋችንን ለማሳደግ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ነን ሲሉም አክለዋል።