በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ በቡሻሻ እና በዎሺ ዎቻ ዳቃያ ቀበሌ አዋሳኝ ቦታ ላይ የሚገኝ የተፈጥሮ መስህብ ስፍራ ነው፡፡
የ‘እግዜር ድልድይ’ ወይንም በወላይትኛ መጠሪያ ‘ጦሳ ዛርጲያ’ በመባል የሚታወቀው ይህ የመስህብ ስፍራ ከኦፋ ወረዳ ዋና ከተማ ገሱባ በ4.5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ስፋቱ 20 ሜትር ርዝመቱ ደግሞ 6 ሜትር ነው፡፡
የተፈጥሮ ድልድዩ ሙሉ በሙሉ ከድንጋይ የተፈጠረ ሲሆን፣ የሁለቱ አካባቢ ሰዎች በአዋሳኝ ስፍራ የሚገኘውን ትልቅ ወንዝ ያለምንም ስጋት እንዲሻገሩ በማድረግ ለዓመታት ሲያገለግል ቆይቷል፡፡
ከድልድዩ ለየት ያለ ተፈጥሮ በተጨማሪ ውኃው ድልድዩን አቋርጦት ሲያልፍ የሚፈጠረው ፏፏቴ ጎብኚዎች አካባቢውን እንዲመርጡት ያደርጋል፡፡
የድልድዩ ዕድሜ ምን ያክል እንደሆነ በውል ባይታወቅም፣ ሰዎች በአካባቢው መደበኛ ኑሮ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ አስከ አሁን ድረስ ይህንን ድልድል ለመሸጋገሪያነት እየተጠቀሙ መሆናቸው ይነገራል፡፡
ይህ ስፍራ ለማኅበረሰቡ በድልድይነት ከሚሰጠው አገልግሎት ባሻገር ሰዎች በእረፍት ቀኖቻቸው ውብ ጊዜን እያሳለፉ በፈጣሪ ሥራ የሚደነቁበት ውብ የተፈጥሮ ስጦታም ነው፡፡
በተመስገን ተስፋዬ
#EBC #ebcdotstream #wolita #nature #bridge