በአማራ ክልል በየደረጃው የሚገኙ ዳኞችና የጉባዔ ተሿሚዎች የተሳተፉበት ከመስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የቆየው የዳኞች ጉባዔ ተጠናቋል።
በማጠቃለያ መድረኩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ለዳኞችና ጉባኤ ተሿሚዎች በሰጡት የሥራ አቅጣጫ፤ የክልሉ መንግስት በክልሉ ጠንካራ የዳኝነት ሥርዓት ለመገንባት ፍላጎት እንዳለውና በዚህም በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የክልሉ የዳኞችና የጉባዔ ተሿሚዎች ጉባኤም የዚሁ የትኩረት አቅጣጫችን አንዱ አካል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ለወደ ፊቱም የዘርፉን ባለድር አካላት የሚያሳትፉ ውይይቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
በዘርፉ የአሠራር ማሻሻያዎችን፣ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን የማሟላት እና መሰል ሥራዎችን የክልሉ መንግስት አጠናክሮ ይሰራል ብለዋል።
ዛሬ በተጠናቀቀው የዳኞች ጉባኤ ከ2 ሺህ 300 በላይ ዳኞችና የጉባዔ ተሿሚዎች ሲሳተፉ ቆይተዋል።
በሳሙኤል ወርቅአየሁ