በቤልጂየም፣ ብራስልስ እየተካሄደ ባለው 2ኛው የግሎባል ጌት ዌይ ፎረም ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ፥ የግሎባል ጌት ዌይ ስትራቴጂ ከኢትዮጵያ የልማት ትልሞች ጋር የሚጣጣም ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው ሁለንተናዊ የተቋማት ሪፎርም ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ኢንቨስትመንት ምቹ እንደሆነ ፕሬዚዳንት ታየ ለጉባኤው ገልጸዋል።
ታዳሽ ኃይል የብልፅግናችን መሠረት እንዲሆን እየሠራን ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ኢትዮጵያ ከ5 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጨውን ታላቁን የሕዳሴ ግድብ በዜጎቿ ርብርብ በራስ አቅም መገንባቷን አንስተዋል።
ግድቡ ለኢትዮጵያውያን እና ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ንጹኅ የኃይል ምንጭ በመሆን ኤሌክትሪክ እንደሚሰጥ አብራርተዋል።
ሕዳሴ ግድብ የማገዶ እንጨት በመሸከም ጀርባቸው ለጎበጠ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እናቶች ረፍት የሚሰጥ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ከፎረሙ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር የታዳሽ ኃይል ምንጭን ለማስፋፋት እና ዘላቂ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ዲጂታላይዜሽንን እውን ለማድረግ በትብብር ለመሥራት ከስምምነት ላይ ደርሳለች።
በመሐመድ ፊጣሞ
#ebcdotstream #globalgatewayforum #Brussels