Search

በአማራ ክልል የተቀናጀ የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ

ዓርብ መስከረም 30, 2018 53

በአማራ ክልል 3ኛው ዙር የተቀናጀ የልጅን ልምሻ (ፖሊዮ) መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጀምሯል፡፡
ክትባቱ በክልሉ በአንዳንድ አካባቢዎች የልጅነት ልምሻ በሽታ በመገኘቱ ለወረርሽኙ ምላሽ ለመስጠት የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ክትባቱ ከዛሬ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ነው፡፡
በክልሉ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሕጻናት ክትባቱን ለመስጠት በዕቅድ መያዙም ተገልጿል።
ክትባቱ ቤት ለቤት፣ በትምህርት ቤቶች እንዲሁም በጤና ተቋማት የሚሰጥ ሲሆን ህብረተሰቡ ከ10 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናትን የፖሊዮ መከላከያ ክትባት እንዲያስከትብ ጥሪ ቀርቧል።
በክልሉ ክትባቱ እየተሰጠ የሚገኘው ደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ እንዲሁም ጎንደር ከተማ ላይ በተወሰደ ናሙና የልጅነት ልምሻ በሽታ መገኘቱ በላቦራቶሪ በመረጋገጡ መሆኑን በአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር አብርሃም አምሳሉ ተናግረዋል።
ክትባቱ እየተሰጠ የሚገኘውም በሽታው በተገኘባቸው አጎራባች በሆኑ በ8 ዞኖችና በ58 ወረዳዎች መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
 
በሳሙኤል ወርቅአየሁ