Search

በአፋር ክልል የተቀናጀ የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ

ዓርብ መስከረም 30, 2018 53

በአፋር ክልል 3ኛው ዙር የተቀናጀ የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) መከላከያ ክትባት በክልሉ በሁሉም ወረዳዎች እና ከተማዎች ዘመቻ ተጀምሯል፡፡
ክትባቱ ከዛሬ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ነው፡፡
በክልሉ ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ 349 ሺህ 73 ለሚሆኑ ሕፃናት ክትባቱን ለመስጠት መታቀዱ ተመላክቷል፡፡
ክትባቱ ቤት ለቤት፣ በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማት እና የአርብቶ አደር ማህበረሰብ በሚገኝበት በየ ገጠሩ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።
የክትባት ዘመቸው የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ያሲን ሀቢብን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሎጊያ ጤና ጣቢያ ተጀምሯል።
 
በሁሴን መሐመድ