Search

በኢትዮጵያ የሳይበር ጥቃቶችን መመከት የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ነው

ቅዳሜ ጥቅምት 01, 2018 49

በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት እና አስተማማኝ የቴክኖሎጂ ዕድገትን እውን ለማድረግ የሳይበር ደህንነት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ገለጹ።

ኃላፊዋ ይህን ያሉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር 6ኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ባስጀመሩበት መድረክ ነው።

90 ሚሊዮን የስልክ ተጠቃሚዎች እና 50 ሚሊዮን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ባሉበት ሀገር ውስጥ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ካልጎለበተ በሀገር ላይ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑንም ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ተናግረዋል።

በሁሉም ዘርፍ የመንግሥት የልማት እንቅስቃሴ በተጠናከረበት በዚህ ወቅት የልማት ፕሮጀክቶች የሳይበር ተጋላጭነት ስጋቶችም እየበረከቱ ነው ያሉት ደግሞ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ ናቸው።

የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶችን መመከት የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ በቀጣይ የዜጎችን የሳይበር ግንዛቤ ለማጎልበት ሥራዎች ይከናወናሉ ሲሉ ተናግረዋል።

በቀጣይ የሚተገበረውን ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት የሳይበር ደህንነት ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ፤ የሚመለከታቸው ሁሉ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

በፍሬሕይወት ረታ

#ebcdotstream #ethiopia #cybersecurity