Search

ፖላንድ በዲጂታላይዜሽን የአውሮፓ መሪ የሆነችበት ተሞክሮ

እሑድ ጥቅምት 02, 2018 82

ዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን ወጪና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ለመፈፀም ከማስቻሉም በላይ ስራዎች በቴክኖሎጂ የታገዙ በመሆናቸው ሙስናን ለመከላከል ብክነትን ለማስቀረት ትልቅ ሚና አለው፡፡

ፖላንድ ባለፉት 30 ዓመታት በዘርፉ ያከናወነችው ስር ነቀል ስራ የዜጎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ፣ ሀገራዊ እድገቷን በእጅጉ በመቀየር በዘርፉ የአውሮፓ መሪ እንድትሆን ያስቻላት ጉዳይ ነው፡፡

አንድ የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም 10 ሚሊየን ዜጎች የኦንላይን አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ በአውሮፓ የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የቴክኖሎጂው እምብርት ወይም ነብር የሚል ሲያሜም አግኝታለች፡፡

ሀገሪቱ ከህዝቧ አንድ ሶስተኛ ወይም 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቿን በአንድ የሞባይል መተግበሪያ ዋና ዋና መንግስታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ማድረጓ ከሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ተለይታ ቀዳሚ ስፍራ ላይ እንድትገኝ አስችሏታል፡፡

ቴክኖሎጂው መታወቂያ ካርድ፣ የንግድ ፍቃድ፣ የአሽከርካሪ መንጃ ፍቃድ ለማውጣት፣ የአየርና የባቡር ትራንስፖርት ቲኬት ለመቁረጥ፣ ማንኛውንም ግብይት እና ፓኬጆችን ግዥ ለመፈፀም እንዲሁም አዲስ የኦንላይን ስራ ለመጀመር ያስችላል፡፡

ፖላንድ ቴክኖሎጂውን በማዘመን ከ10 ሰዎች 9ኙ የሞባይል ባንኪንግን አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉና ፈጣንና የድህንነት ስጋት የሌለበት አስተማማኝ የኦንላይን አገልግሎት መስጠት መቻሏ ከብዙዎቹ የአውሮፓ ሀገራት ቀዳሚ ያደረጋትና ለለሌች ሀገራትም እንደተሞክሮ የሚወሰድ ነው፡፡

ዜጎች ስለ ዲጅታል ቴክኖሎጂው አጠቃቀም በቂ እውቀት እንዲኖራቸው በኦንላይን በነፃ ትምህርት ማግኘት የሚችሉበትም እድልንም ሀገሪቱ ፈጥራለች፡፡

ፖላንድ እ.ኤ.አ በ2035 85 በመቶ የሀገሪቱ ዜጎች መሰረታዊ የዲጅታል ቴክኖሎጂ እውቀት እንዲኖራቸው፣ ሁሉም የፐብሊክ ተቋማት ዲጅታል ኤሌክትሮኒክ ዶክመንት ተግባራዊ ለማድረግ፤ 20 ሚሊዮን የፖላንድ ዜጎች ዲጅታል መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ ተግታ እየሰራች ትገኛለች፡፡

በላሉ ኢታላ

#ebc #ebcdotstream #Poland #Digitisation