Search

የፍርድ ቤት አገልግሎትን ዲጂታላይዝ ማድረግ ግልፅ የፍትሕ ሥርዓትን ለመገንባት ያግዛል

ረቡዕ ጥቅምት 05, 2018 43

የፍርድ ቤት አገልግሎትን ዲጂታላይዝ ማድረግ ፍትሐዊ እና ግልፅ የፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት እንደሚያግዝ የፌዴራል ጠቅላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ዳኛ አበበ ሰለሞን ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው ከኢቲቪ አዲስ ቀን የሀገር ጉዳይ መሰናዶ ጋር በነበራቸው ቆይታ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀገር አቀፍ ደረጃ የአገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታላይዝ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
ይህም የዳኝነት አሰራርን በማዘመን ቀልጣፋ እና ተዓማኒ ሥራዎችን ለመስራት እንደሚያግዝ ነው የተናገሩት፡፡
ፌዴራል ፍርድ ቤቶችን በራሳቸው ኔትወርክ የማስተሳሰር እና አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ መሰረታዊ ሥራ መሰራቱን እና መተግበሪያዎች መልማታቸውን ገልጸዋል፡፡
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ስዩም መንገሻ በበኩላቸው፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ከታለመ ጀምሮ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን አንስተዋል፡፡
በርካታ የመንግሥት ተቋማት የዲጂታል አሰራርን በማበልጸግ ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ ይህም ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ምቹ እና ቀልጣፋ እንዳደረገውም ነው የገለጹት፡፡
ወረቀት አልባ ቴክኖሎጂን በማጎልበት መረጃዎች በአግባ እንዲያዙ እና ቀልጣፋ አሰራር እንዲፈጠር አስችሏል ብለዋል፡፡
በሜሮን ንብረት